Visit Dawuro

Visit Dawuro

መዳረሻዎች /    Destinations

ማራኪ ቦታዎችን ይጎብኙ/Go fascinating Places

ሙዚየም

200 ጎብኝዎች

ግልገል ጊቤ

736 ጎብኝዎች

ሃላላ ኬላ

234 ጎብኝዎች

ጨበራ ጩርጩራ ፓርክ

1567 ጎብኝዎች

ኮይሻ

284 ጎብኝዎች
       

አሁን የጉዞ ቲኬትዎን ዪቁረጡ

ይደዉሉ: +251118619695

ይወቁን / Get to know us

የንጉስ ሀላላ ድንጋይ ካቢ

ከአምስት መቶ ዓመት በላይ እድሜን ያስቆጠረው ካብ አንድ ዙር ርዝመት 170 ኪሎ ሜትር በላይ የሚረዝም ነው፡፡ በዚህ ርዝመቱ የጎፋ፣ የወላይታን፣ የካፋንና የጅማን ድንበር በሙሉ ያካልላል፡፡ የድንጋዩ ካብ ስራ ከ1582 እስከ 1607 ባለው ጊዜ የተሰራ ሲሆን በተለይም በወላይታ በከምባታና በጎፋ ወሰን ያለው ግዙፍ እና ረዥሙ ካብ ከኤሌ እስከ ዛባ ጋራባ የተዘረጋው ነው፡፡ ይህግንብ ከሁለት ሜትር ተኩል እስከ ሶስት ሜትር የሚደርስ ቁመት ሲኖረው ከሁለት ሜትር ተኩል በላይ የጎን ስፋት አለው፡፡


       

አሁን የጉዞ ቲኬትዎን ዪቁረጡ

ይደዉሉ: +251118619695

ማንቻላ

ማንቻላ የዳውሮ ብሔር የዕዴ ጥበብ ሥራ ውጤት ስሆን ባህላዊ የቆዳ ምንጣፍ ነው፡፡ ማንቻላ በዳውሮ ለተለያዩ አገልግሎቶት የሚውል ስሆን በጋብቻ ጊዜ እንደስጦታ የሚሰጥ፣ ለነገስታትና ለሹማምንቶች አንድሁም ለክብር እንግዳዎች ለመኝታ የሚነጠፍ ምንጣፍ ነው፡፡ ማንቻላ የሃላላ ድንጋይ ካቢ፣ ባህላዊ የዳውሮ አስተዳደራዊ መዋቅርና የንጉሱ ስልጣንን የሚያሳይ በባህላዊ ጥበብ የተሳለ ትርጉም ያለው የዕደ ጥበብ ሥራ ነው፡፡


       

አሁን የጉዞ ቲኬትዎን ዪቁረጡ

ይደዉሉ: +251118619695

ኮራንቶ ፏፏቴ

ፏፏተው ከአሰገራም ተፈጥሮ በግምት 150 ሜ. በላይ ከፍታ የሚወረድ ለውቧ ዳዉሮ ተፈጥሮ የቸረላት ቱሪስት መዳረሻ ለጎበኚ ወይም ለተመራማር ልዩ ስሜት የሚፈጥር ማራኪ ምድረ-ገነት ተምሳሌት ፏፏቴ ነው፡፡ የሚገኘውም በሎማ ቦሳና ዲሣ ወረዳ መካከል ከገሣ 22 ኪ.ሜ ርቀት በሚዳ-ዛሎና በኮይሻ ማህበረሰብ ተጠብቆ የቆየ ቱሪዝም ሀብት ነው፡፡ በቱሪስት የሚጎበኝ ቀልብ የሚስቡ ለሎች መዳረሻዎች በአቅራቢያው ተያያዥ መስህቦች፤ባሌሰንሰለታማ ተራራ፤ የማታ ጥብቅ ደን፣ ያኮማንቲያ ዋሻ ታሪካዊ ይሁን ተፈጥሯዊ ብዙ ጥናትና ምርምር ሥራ የሚፈልግ ድንቅ ዋሻና ታሪካዊ "ሁሉቁዋ" ዋሻ የዳውሮ ንጉስ የማንጻት ሥነ-ሥርዓት የሚየስፈጽምበት ዋሻ ነው፡፡ በዋሻው የባህላዊ እምነት በመጣስ ግብረ-ሥጋግንኙነት ፈጽሞ የተገኘ ሰው ኃጢአትና ሌሎች በባህሉ እርኩሰት ነው የተባሉ ድርግቶችን የማንጻት ሥነ-ሥርዓት ክንዋኔዎች በዳወሮ ነገስታቶች ሥር የት የሚጸምበት መግቢያና መውጫ ያለው ድንቅ ዋሻ ፍፁም ታሪካዊ በሚሰጥ ተፈጥሮ የታጀበ ድንቃድንቅ ስፍራዎችን በአንድ ጉዞ የሚጎበኚ በመሆኑ መሰህቦቹ ለቱሪስቶች ተመራጭ መዳረሻ ናቸው፡፡


       

አሁን የጉዞ ቲኬትዎን ዪቁረጡ

ይደዉሉ: +251118619695

ጨበራ ጩርጩራ ብሄራዊ ፓርክ

በደቡብ ምራዕብ ኢትዮጵያ መንግስት አማካይነት በ1997 ዓ.ም ተካልሏ፡፡ ፓርኩ በዓለም ዝሪያው በመጥፋት ያሉ የአፍርካ ዝሆንና ሌሎች ብርቅዬና ድንቅ የዱር እንስሳት መገኛ ነው፡፡የሚገኝበትም በመካከለኛው ኦሞ ሸለቆ ተፋስስ በዳውሮ ዞንና በኮንታ ልዩ ወረዳ መካከል ይገኛል፡፡ ስፋቱም 1190 ካሬ ኪ.ሜትር ስሆን ከፍታውም ከባሕር ጠለል 700 ሜትር እና 2800 ሜትር መካከል ነው፡፡ በፓርኩ መካከል አቋራጭ በቋሚ ገባር ወንዞች ሻሽማና አድካላ ናቸው፡፡ የውሃ ውስጥ እንስሶች (ዓሣ፤ ዓዞና ጉመሬ) መኖሪያ ሐይቆች ጮፎሬ፤ ሙኑኣ ዎንባ ከርባላ፤ ሽሻ፤ ሾተ ባሄቡሎ ሐይቅና አድባሜ ፍል ውሃ ..ወዘቴ ታርካዊ ሀገር ኩራት የሆኑ ሀብቶች ይገኝበታል፡፡ፓርኩ በተፈጥሮ የተቸሩልን አገር በቀል ዛፎች የአየር ሚዛን የሚጠብቁ በደኖች የተሸፈኔ አከባቢ ነው፡፡ በፓርኩ በተለያዬ ጊዜጥና ትግኝትመነሻ 37 ትላልቅና መካከለኛ አጥቢ የእንስሳት ዝሪያዎች፤ 237 የአእዋፍ ዝሪያዎች እንድሁም በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ የአእዋፍ ዝሪያዎች ፓርኩን ልዩ ያደርጋል፡፡ አጥቢ የዱር እንስሳትም በርካታ የአፍሪካ ዝሆን፤ ጎሽ፤ ጉመሬ፤ ብኾር(ዶጊያ) ከርካሮ፤ድኩላ፤ድፈርሳ፤ ትልቁ አጋዜን፤ ዓሳማ፤ ዝንጅሮ፤ ጦጣ; አንበሳ፤ ነብር፤ ዱር ድመት አነር፤ ጉረዛ…..ወዘቴ. በመኖራቸው ፓርኩን ልዩ ማድረጉ ለቱሪስቶችና ለተመርማሪዎች ተወዳዳሪ ያልተኘ ቱሪስት መዳረሻነት የተመዘገበ ፓርክ በዳዉሮ ዞን በኩል በ3 ወረዳዎች በ11 ቀበለያት የሚያዋስን በኢሠራ ወረዳ 6 ቀበለያት; በከጪ ወረዳ 4 ቀበለያት እና በታርጫ ዙ/ወረዳ አንፃር አንድ ቀበለ አዋሳኝ የሚገኘ የቱሪዝም ሀብት በእንግዳ ወዳድ ሠላም በሰፈነበት ማህበረሰብ በእንክብካቤ የተያዘ ፓርክ በውስጡ ብዙ ማዕድናት የብረት አፈር የወርቅ አፈርና ሬድአሽ በጥናት የተረጋጌጠ እና የተፈጥሮ ግብርና ምርት የጫካ ቡና የጫካ ማር ኮርሩማ ጥምዝ ...ወዘቴ ኦርጋኒክ ምርቶች የበለጸጌ ፓርክ በመሆኑ ለጎበኝዎችና ለተመርማሪዎች ከፍተኛ እርካታ ይሰጣል ኑ ጎበኙ ተመራሙ በአድራሻችን ደውሉ ተጨማሪ እንፎርሜሽን ያገኛሉ፡፡


       

አሁን የጉዞ ቲኬትዎን ዪቁረጡ

ይደዉሉ: +251118619695

ባህላዊ ምግቦች

ሲሊሷ/siillissuwaa/:- ሲሊሷ ወካይ ከሆኑት ዳውሮ ባህላዊ ምግቦች ቀዳሚ ስፍራ የሚይዝ ስሆን አሰራሩም ከተጣራ ቅቤ፣ ዓይብ፣ ነጭ ሽንኩርት፣ አብሽ፣ ኮሮሩማ፣ ቀይ በርበሬ፣ እርድና ጨው ገብቶበትና ቅቤ ከአይብ ወደ ላይ ወተው በወጪት እስክታይ ድረስ ተጨምሮበት ተሰርቶ ለተመጋቢዎች በጣባ ተደርጎ ከቀንድ በተሰራው ባህላዊ ማንኪያ/mook’iya/ እየተዛቄ በቆጮ ቅጣ፣ በበቆሎ ቅጣ፣ በጤፍ ቅጣ፣….ወዘተ ቅጣዎች ጋር ተምጎ የምበላ ጣፋጭ ምግብ ነው፡፡ ኡታ/uttaa/፡- ሲሊሷን ቀጥሎ በጣም የምታወቅ ጣፋጭ ባህላዊ ምግብ ነው፡፡ ኡታ የሚዘጋጀው ከጤፍ ቅጣ፣ ከቦቆሎ ቅጣ፣ ከዘንጋዳ ቅጣ፣ ከስራስር ምግቦች፣ ከዓይብ፣ ከቅቤ እና በርቤረ ሳይገባ ከተለያዩ ቅመማቅመሞች የሚዘጋጅ ምግብ ነው፡፡ ኡታ በአብዘኛው ጊዜ የመበላሸት አቅሙ ዝቅተኛ ስለሆነ ለረዥም መንገድ ተጓዥ ነጋዴዎች ለስንቅ በዋናነት የሚዘጋጅና ለክብር እንግዶች፣ ለተገራዦች፣ ለክብረ-በዓላት፣ ለቤተሰብ፣ ለአራስ እናቶች፣ ለሰርገኞች፣. . ወዘተ በሰፍው ይዘጋጃል፡፡ ኡታ ከአሰራሩም አንፃር የበቆሎ ኡታ፣ የጠፍ ኡታ፣ ኡሹሺያ ኡታ/ሼሊያ/፣ አሹዋ ኡታ/ፓቲያ ኡታ/፣ ዩዲያ ኡታ፣ቦይያ ኡታ፣ማልዶዋ ኡታ፣. . . ወዘተ የምባል ስያሜ ይኖረዋል፡፡ ታንጯ (tanc’c’uwaa)፡- ታንጯ የሚዘጋጀው ከጎመን፣ አይብ፣ ቅቤ፣ እና ከተለያዩ ቅመማ ቅመሞች ሆኖ አሰራሩም የተቀቀለ ጎመን በደቃቁ ይከተፍና በድስት ተጨምሮ አይብ፣ የተነጠረው ቅቤ እና የተለያዩ ቅመማ ቅመሞች በደንብ ተጨምሮበት ተሰርቶ ለመበያነት ቀርቦ በቅጣ ተሚጎ የምበላ ነው፡፡

Trips
& tours

ዳውሮን ለምን ይመርጣሉ

የዳውሮ ዞን ከአዲስ አበባ በሻሸመኔ ወላይታ ሶዶ 455 ኪ.ሜ ከአዲስ አበባ በጅማ 479 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ እንዲሁም 38 በመቶ ቆላማ፣ 41 በመቶ ወይናደጋና 21 በመቶ በደጋ እንደተሸፈነ ይገመታል፡፡ ዓመታዊ አማካይ የዝናብ መጠን ከ1374.2 እስከ 2271.6 ሚሊ.ሜትርና አመታዊ የሙቀት መጠን ከ15-10c-27.50c ድግሪ ሴንቲ ግሬድ ይደርሳል፡፡

  • የመጓጓዣ እና የሎጂስቲክስ ዘዴዎች

    ወደ ዳውሮ ለሚመጡ ጎብኝ ቤተሰቦቻችን በአውሮፕልን እስከ አርባ ምንጭ ወይም ሃዋሳ ድረስ በመምጣት በምቹ መንገዱ ተፈጥሮን እየጎበኙ መምጣት ይችላሉ፤ እንዲሁም በመኪና ለምትመጡ በአርባምንጭ ወይም በሃዋሳ ወይም በጅማ በተምቸዎት መንገድ መምጣት ይችላሉ

  • Get Instant Tour Bookings

    ውድ ቤተሰቦቻችን ወደ ዳውሮ ሲመጡ ከቤትዎ ወደ እቤትዎ እንደመጡ እንዲሰማዎት በማድረግ ሃሳብዎን እንዲቀለዎ የሚያደርግ ተፈጥሮን በማየት ዘና ዪላሉ።